በኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት በክብርት ሳህለ ወርቅ ዘውደ የተመራ የአገራችን ልዑካን ቡድን በሜይ 29/2023 በተከበረው በናይጄሪያ ፕሬዝዳንት በክቡር ቦላ አህመድ ቲንቡ በዓለ ስመት ላይ የተገኘ ሲሆን ኩነቱ የሁለቱን አገራት ሁለትዮሽ ግንኑነት ለማጠናከር መልካም አጋጣሚ የፈጠረ ነበር።
በበዓለ ስመቱ ዝግጅት ላይ ክብርት ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውደ የጎንዮሽ ውይይቶችን ከናይጄሪያ አዲሱ ፕሬዝዳንት ከክቡር ቦላ አህመድ ቲኒቡ ጋር በሁለቱ አገራት መካከል ያለዉ ታሪካዊ የባይላተራል ግንኙነት ይበልጥ ስለሚጠናከረበት ሁኔታ ውይይት አድርገዋል ፡፡እንዲሁም ከኮትዲቯር ፣ ከታንዛኒያ እና ከሳኦቶሚና ፕሪንሲፐ ፕሬዝዳንቶች ፣ ከኢኳቶሪያል ጊኒ ምክትል ፕሬዝዳንት እና ከአውሮፓ ሕብረት፣ ከአሜሪካ፣ አና ሳውዲ አረቢያ ወዘተ አገራት ተወካዮች ጋር በሁለትዮሽና በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ውይይቶች አድርገዋል።
በተጨማሪም በዓለም አቀፍ ደረጃ ትላልቅ ኢንበስትመንት የማድረግ አቅም ካላቸው የናይጄሪያና የሌሎች አገራት አንከር ኩባኒያዎች ተወካዮች ጋር ውይይት አደርገዋል። እንዲሁም በአቡጃና አካባቢው ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጋር ኤምባሲው ባዘገጀው የውይይት መድረክ ላይ ሁሉም የኮሚኒቲ አባላት ለሃገራቸው አምባሳደር መሆን እንዳለባቸውና በሚኖሩበት አገር ያገኙትን ገንዘብ፣ እውቀትና ልምድ በአገራችን እንበስት ማድረግ እንዲችሉ አሳስበዋል።