የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ እና የኢፌዴሪ ቀዳማዊት እመቤት ክብርት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው የተገኙበት ከፍተኛ የልዑካን ቡድን እ.ኤ.አ ሜይ 25 እስከ 26 ቀን 2022 በናይጄሪያ ይፋዊ የስራ በጉብኝት እድርጓል ፡፡ የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ክቡር ሙሃመዱ ቡሃሪ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ እና ልዑካናቸው አቡጃ ሲደርሱ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ እና ልዑካናቸው ከናይጄሪያ ልዑካን ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል። ሁለቱ እህትማማች አገሮች ትብብራቸዉ ስለሚጠናከርብት ሁኔታ መክረዋል ፡፡በአህጉራዊ እና በአለም አቀፍ ደረጃ በጋራ ጉዳዮች ዙሪያ ተባብረዉ ለመስራት ተሰማምተዋል፡፡